Phone Number: +251 9 938 2848 | Email Address: info@ethioafricraising.com
የጥምረት ለሴቶች ድምፅ 10 ሴቶችን የተመለከቱ አጀንዳዎች ለሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አስረከበ

ሰኔ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጥምረቱ በ10 ክልሎች እና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች ከ6 ሺህ 122 በላይ የሴት የማኅበረሰብ ተወካዮችን በመድረስ ከ3 ሺህ 500 በላይ አጀንዳዎችን ሰብስቧል።
ከ10 አጀንዳዎች መካከልም
በሴቶች እና ሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ ጸታዊ ጥቃቶች እና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መባባስ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶችእና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እየጨመሩ ሲሆን፣ የፍትሕ እጦት እና በአጥፊዎች ላይ የቅጣት አፈጻጸም ክፍተት የችግሩ ሰለባዎችን ለከፋ መከራ እየዳረገ ነው።
ይህ አጀንዳ እነዚህን ጥቃቶች ለመግታት እና ፍትሕን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የሕግ እና ማኅበራዊ ማእቀፎች እንዲተገበሩ፤
የሰላም እጦት እና የፖለቲካ
አለመረጋጋት በሴቶች ላይ የሚፈጥረው ችግር:- የሰላም እጦት እና የፖለቲካ አለመረጋጋት ሴቶችን ለአስገድዶ መድፈር፣ ለመፈናቀል፣ ለምግብ እና መጠለያ እጦት እንዲሁም ለሥነ ልቦና እና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች እያጋለጠ ነው። በዚህም ምክንያት የሴቶችን መብቶች የሚጠብቁ ሕጎች፣ ደንቦች እና ፖሊሲዎች ተግባራዊ መሆን አለመቻላቸው የሴቶችን ደኅንነት አደጋ ላይ ጥሏል።
ለሴት አካል ጉዳተኞች የሚሰጠው ትኩረት ማነስ
የሴት አካል ጉዳተኞች ለተደራረቡ ችግሮች የተጋለጡ ሲሆኑ፣ ተቋማዊ መሠረተ ልማቶች ለእነሱ ምቹ አለመሆናቸው እና በሥራ እድል፣ በፖለቲካ ተሳትፎ እና በመርጃ መሣሪያዎች በቂ ትኩረት አለማግኘታቸው ተጠቃሽ ናቸው። ይህ አጀንዳ ለሴት አካል ጉዳተኞች የሚሰጠው ድጋፍ እና ትኩረት እንዲጨምር ይጠይቃል።
የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ እና ውሳኔ ሰጭነት ሚና ማነስ:- በኢትዮጵያ የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ እና የውሳኔ ሰጭነት ሚና አናሳ ነው። ሴቶች በአመራርነት እና በውሳኔ ሰጭነት ቦታዎች ላይ በቂ ውክልና ስለሌላቸው፣ የሕግ አውጭ፣ ሕግ አስፈጻሚ እና ሕግ ተርጓሚ አካላት ውስጥ 50 በመቶ ውክልናቸው እንዲረጋገጥ ተጠይቋል።
የሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እና የመሬት ባለቤትነት መብት ውስንነት:- ሴቶች በኢኮኖሚው ዘርፍ ያላቸው ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ዝቅተኛ ነው። በተለይም በግብርና እና በንግድ ዘርፍ የመሬት፣ የብድር እና የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ውስንነት ያጋጥማቸዋል፣ እንዲሁም ከሀብት ክፍፍል ጋር በተያያዘ የአድልሎ ሰለባ ይሆናሉ። የሚሉት ጥቂቶቹ ሲሆኑ አማራና ትግራይ ክልሎች በዚህኛው አጀንዳ ማሰባሰብ ላይ አለመካተታቸዉ ተመላክቷል፡፡
Newa Ethiopia Ethiopian Women Lawyers AssociationEthiopian Women Rights Advocate – EWRAELiDA EthiopiaADDIS ABABA Women’s AssociationEthiopian Human Rights Defenders Center-EHRDCEthiopian Human Rights CouncilLawyers For Human RightsCenter for Advancement of Rights and Democracy – CARDACDD – Advocacy Center for Democracy & Development
See less